ነሐሴ
12 ታሪካዊ ቀን ናት፤ በዚች ቀን በኢትዮጵያ ታሪክ ጉልህ ስፍራ ያላቸው ግለሰቦች ተወልደዋልና፡፡ በተለያዩ ዓመታት ቢሆንም ንጉሰ ነገሥት ዳግማዊ አፄ ምኒልክ፣ እቴጌ ጣይቱ ብጡል እና ፊታውራሪ ገበየሁ የተወለዱት ነሐሴ 12 ቀን ነው፡፡
በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ከፍ ያለ ቦታ ይዘው የሚገኙት ንጉሰ ነገሥት ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ነሐሴ 12 ቀን 1836 ዓ.ም ሸዋ አንጎለላ ውስጥ ተወለዱ፡፡ አባታቸው ንጉሥ ኃይለመለኮት ሳህለሥላሴ ሲሆኑ እናታቸው ደግሞ ወይዘሮ እጅጋየሁ ለማ ይባላሉ፡፡ ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ ሸዋን ለማስገበር ከጎንደር ወደ ሸዋ በሄዱበት ወቅት ንጉሥ ኃይለመለኮት ታመው ሲሞቱ ንጉሰ ነገሥቱ ልጅ ምኒልክን ወደ መቅደላ ይዘዋቸው ተመለሱ፡፡ ከስምንት ዓመታት ቆይታ በኋላ፣ በ1857 ዓ.ም ከመቅደላ አምልጠው ሸዋ ገቡ፤የአባታቸውን የንጉሥ ኃይለመለኮት ሳሕለሥላሴ አልጋ ወረሱ፡፡
ጥቅምት 25 ቀን 1882 ዓ.ም ደግሞ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገሥት ሆኑ፡፡ ንጉሰ ነገሥት ዳግማዊ አጤ ምኒልክ በዘመናቸው ስላከናወኗቸው ተግባራት በዚች ጽሑፍ ውስጥ ለመዘርዘር መሞከር ፈፅሞ የማይታሰብ ነው፡፡ ኢትዮጵያ አሁን ያላትን ቅርፅ እንድታገኝ ከማድረግ ጀምሮ በወራሪዎች ላይ ድል በመቀዳጀትና የስልጣኔ በረከቶች ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ በማድረግ የሰሩት ስራ በዋጋ የማይተመን ነው፡፡ የታሪክ ምሁራን ስለ ንጉሰ ነገሥቱ ከፃፏቸው በርካታ ድርሳናት በተጨማሪ፣ በወቅቱ የነበሩ ታላላቅ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃንም ስለ ንጉሰ ነገሥቱ አውርተዋል፤ጽፈዋል፡፡
የንጉሰ ነገሥት ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ባለቤት፣ እቴጌ ጣይቱ ብጡል በኢትዮጵያ የፖለቲካ፣ የማኅበራዊ እና የሃይማኖታዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ድርሻ እና አስተዋፅኦ ያላቸው ሴት ናቸው። ጣይቱ ብጡል ነሐሴ 12 ቀን 1832 ዓ.ም ደብረ ታቦር ውስጥ ተወለዱ፡፡ ገና ልጅ ሳሉ አባታቸው ደጃዝማች ብጡል ኃይለማርያም በጦርነት ሞቱባቸው። ከዚያም ወደ ጐጃም መጥተው በደብረ መዊዕ ገዳም ገብተው በዘመኑ ይሰጥ የነበረውን ትምህርት በሚገባ ተከታትለው መማራቸው ይነገራል። ፅህፈትን፣ ንባብን፣ ግዕዝና አማርኛ ቅኔን፣ ታሪክን እና የመሳሰሉትን ጉዳዮች በሚገባ ተምረው አጠናቀዋል።
እቴጌ ጣይቱ የዘር ሐረጋቸው የሚመዘዘው ከኢትዮጵያ ነገስታት ተዋረድ ውስጥ በመሆኑ በስርዓትና በእንክብካቤ ያደጉ ናቸው። ትምህርትም በመማራቸውና በተፈጥሮም በተሰጣቸው የማሰብና የማስተዋል ፀጋ በዘመናቸው በእጅጉ የታወቁ ሴት ሆኑ። ስለ እርሳቸውም ዝና በየቦታው ይወራ ነበር። ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ ወደ ሸዋ ዘምተው ልጅ ምኒልክን (በኋላ ዳግማዊ አፄ ምኒልክ) ማርከው ወደ ጐንደር ወስደው በሚያሳድጓቸው ወቅት፣ ምኒልክ በተለያዩ ሰዎች አማካይነት ጣይቱ ስለምትባል ሴት ብልህነትና አርቆ አሳቢነት ወሬ በተደጋጋሚ ይሰሙ ነበር። ‹‹ጣይቱ ማን ናት? ምን አይነት ሰው ናት?›› እያሉ ልባቸው መንጠልጠል ጀመረች።
ልጅ ምኒልክ (በኋላ ዳግማዊ አፄ ምኒልክ) ከመቅደላ አምልጠው ሸዋ በገቡ በ18ኛው ዓመት፣ ሚያዚያ 25 ቀን 1875 ዓ.ም በአንኮበር መድሐኒያለም ቤተ-ክርስትያን ከጣይቱ ብጡል ጋር በቁርባን ጋብቻውን ፈፀሙ። ከአምስት ዓመታት በኋላም፣ ንጉሥ ምኒልክ በ1882 ዓ.ም የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገሥት ሲሆኑ፣ ባለቤታቸው ጣይቱም ‹‹እቴጌ ጣይቱ ብጡል ብርሃን ዘኢትዮጵያ›› ተባሉ፡፡ ጥንዶቹ ከተጋቡ ጀምሮ የአስተዳደር ስራን በምክክር ይሰሩ እንደነበር ታሪክ ያስረዳል፡፡ ነጋድራስ አፈወርቅ ገብረኢየሱስ (ፕሮፌሰር) ‹‹አጤ ምኒልክ›› በተሰኘው መፅሐፋቸው ‹‹የሸዋ ቤተ-መንግሥት ዓለሙ የዚህን ቀን ተጀመረ። የሸዋ ቆሌ፣ የሸዋ ደስታ የዚህን ቀን ተጀመረ። የሸዋ መንግሥት ከጣይቱ በኋላ ውቃቢ ገባው፤ ግርማና ውበት ተጫነው፤ ጥላው ከበደ፤ የእውነተኛው አዱኛ፣ የእውነተኛው ደስታ ከጣይቱ ብጡል ጋር ገባ›› በማለት ስለ ጣይቱ ጽፈዋል፡፡
ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ኢትዮጵያን ለማዘመን በተነሱበት ጊዜ የእቴጌ ጣይቱ እገዛ እና ተጨማሪ ሃሳቦች ጥርጊያውን በሚገባ አፀዳድተውታል። ጣይቱ ያልተሳተፉበት ልማት አልነበረም። የስልኩ፣ ባቡሩ፣ ኤሌክትሪኩ፣ ፊልሙ፣ ውሃው፣ መኪናው፣ ት/ቤቱ፣ ሆስፒታሉ፣ ሆቴሉ፣ መንገዱ ወዘተ መገንባት እና መተዋወቅ ሲጀምር ጣይቱ የባልተቤታቸው የዳግማዊ አፄ ምኒለክ ቀኝ እጅ ነበሩ።

እቴጌ ጣይቱ
እቴጌ
ጣይቱ
በሰው
ልጆች
ታሪክ
ውስጥ
ሕያው
አድርጓቸው በየትኛውም ዘመን እንዲጠሩ ካደረጓቸው ነገሮች መካከል የጥቁር ህዝቦች ሁሉ አበሳ የነበረውን የቅኝ አገዛዝ ስልትን ‹‹አሻፈረኝ››› ብለው ጦርነት ገጥመው በድል ያጠናቀቁበት ታሪክ ነው። ኢጣሊያ ኢትዮጵያን የቅኝ ግዛት አካሏ የማድረግ የረጅም ጊዜ እቅዷን ለማሳካት የጫረችው የዓድዋ ጦርነት በድል እንዲጠናቀቅ እቴጌ ጣይቱ የበኩላቸውን ሚና ተወጥተዋል፡፡ ሚያዚያ 25 ቀን 1881 ዓ.ም አምባሰል ውስጥ በንጉሥ ምኒልክ (በኋላ ዳግማዊ አፄ ምኒልክ) እና በኮንት ፒየትሮ አንቶኔሊ መካከል የተፈረመው ስምምነት ደብቅ የኢጣሊያ ሴራ እንዳለው ሲታወቅ ለተበሳጨው የስምምነቱ ፈራሚ አንቶኔሊ ‹‹ያንተ ፍላጐት ኢትዮጵያ በሌላ መንግስት ፊት የኢጣሊያ ጥገኛ መሆኗን ለማሳወቅ ነው። ነገር ግን ይህን የመሰለው የምኞት ሃሳብ አይሞከርም! እኔ ራሴ ሴት ነኝ። ጦርነት አልፈልግም። ነገር ግን ይህን ውል ብሎ ከመቀበል ጦርነትን እመርጣለሁ!›› በማለት በአገራቸው እንደማይደራደሩ ቁርጡን ነገሩት፡፡
ከዚያም ጦርነቱ አይቀሬ ሆኖ ውጊያው ሲደረግ ብዙ ሺ እግረኛና ፈረሰኛ ጦር እየመሩ ከዳግማዊ አጤ ምኒልክና ከሌሎች የዓድዋ ጀግኖች ጋር ሆነው ዘምተው በኢጣሊያ ሠራዊት ላይ ድል ተቀናጁ። በተለይ ደግሞ የዓድዋው ውጊያ ከመካሄዱ ቀደም ብሎ መቐለ ላይ መሽጎ የነበረው የኢጣሊያ ጦር በውሃ ጥም ምሽጉን ለቆ እንዲወጣ የተገደደበትን ሃሳብ ያፈለቁት እቴጌዋ ነበሩ፡፡
ይህችን ሀገር ከቅኝ ገዢዎች መንጋጋ ፊልቅቆ በማውጣት በጦርነት ውስጥ ገናን ስም እና ዝና ያላቸው እቴጌ ጣይቱ መንፈሳዊት ሴትም እንደነበሩ ታካቸው ያስረዳል። በዓድዋ ጦርነት ዝግጅት እና በጦርነቱ ዘመቻ ወቅትም ማታ ማታ በፀሎት ከፈጣሪያቸው ዘንድ እየተማፀኑ ሀገራቸውን ነፃ ለማውጣት ፈጣሪም አብሯቸው እንዲሰለፍ ይማፀኑ እንደነበር በርካታ ፀሐፊያን ገልፀዋል። እቴጌ ጣይቱ ጦርነቱን በመንፈስም በነፍጥም ነበር ያካሄዱት። ‹‹ሐገረ ኢትዮጵያ ከሌለች ሃይማኖቷም የለም›› ብለው የሀገሪቱ ታቦታት ወደ ዓድዋ እንዲዘምቱ በማድረግም ተፅዕኖ ፈጣሪ ነበሩ።

ፊታዉራሪ ገበየሁ ገቦ
በኢትዮጵያ
የፖለቲካ፣ የማኅበራዊ እና የሃይማኖታዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ድርሻ እና አስተዋፅኦ ያላቸው እቴጌ ጣይቱ ብጡል በዘመናቸው ሀገራቸው ኢትዮጵያን ከቅኝ አገዛዝ አፋፍ ላይ በደረሰችበት ወቅት በቆራጥነትና በአይበገሬነት ተጋፍጠው ትውልድን እና ሀገርን ከመታደጋቸው በተጨማሪም ዛሬ ‹‹የአፍሪካ መዲና›› ተብላ የምትጠራውን አዲስ አበባን የመሠረቱ የግዙፍ ስብዕና ባለቤትም ናቸው። በእስራኤል ውስጥ በተለይም በእየሩሳሌም ውስጥ ያለውን የዴር ሱልጣን ገዳምን በመርዳት እና የኢትዮጵያ መሆኑን አስረግጠው ያስመሰከሩ ሃይማኖተኛ ና ፖለቲከኛ ነበሩ። ኢትዮጵያ በጦርነቱም፣ በስልጣኔውም፣ በፖለቲካውም፣ በመንፈሳዊ ውም ዓለም ጠንክራ እንድትወጣ ብዙ ብዙ ጥረዋል፤ ተሳክቶላቸዋልም።
ንጉሰ ነገሥት ዳግማዊ አፄ ምኒልክ በ1906 ዓ.ም ሲያርፉ መኳንንቱና መሳፍንቱ እቴጌ ጣይቱ የነበራቸውን ተፅዕኖ ያውቁ ስለነበር የኃይል ሚዛኑ ወደ እቴጌዋ ዘመዶች ወደ ጎንደር ይሄዳል ብለው በመስጋት ብርቱዋን ሴት ከቤተ-መንግሥት ገለል አደረጓቸው፡፡ በመጨረሻም የካቲት 4 ቀን 1910 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡
እቴጌ ጣይቱ ቅኝ አገዛዝን ተዋግተውና ድል አድርገው ሀገርን በነፃነት በማቆየት ሂደት ውስጥ በዓለም የሴቶች ታሪክ ውስጥ ትልቅ ስፍራ የሚሰጣቸው ሴት እንደሆኑ በርካታ የውጭና የአገር ውስጥ ፀሐፊዎችና ምሁራን ገልጸዋል፡፡
የዓድዋው ጀግና ፊታውራሪ ገበየሁ (አባ ጎራ) የተወለዱትም ነሐሴ 12 ቀን ነው፡፡ የንጉሰ ነገስቱ የመሐል ጦር አዛዥ የነበሩት ፊታውራሪ ገበየሁ ከጣልያኖች ጋር በተደረጉ በሁሉም ጦርነቶች ጀግንነታቸውን ያስመሰከሩ አገር ወዳድ ሰው ነበሩ፡፡ ዋነኛው የኢትዮጵያና የኢጣሊያ ጦርነት ዓድዋ ላይ ከመካሄዱ ቀደም ብሎ አምባላጌ ላይ በተደረገው ውጊያ የአምባላጌውን ምሽግ በመስበር በጣሊያን ላይ የመጀመሪያውን የድል ደወል ያሰሙትና ዋናው የድሉ ባለቤት እርሳቸው ነበሩ፡፡ በዚህም ምክንያት በወቅቱ የፈረንሳይ ጋዜጦች ‹‹የአምባላጌው የኢትዮጵያ ጀግና›› በማለት እንዳወደሷቸው አንጋፋው የታሪክ ፀሐፊ አቶ ተክለፃዲቅ መኩሪያ ጽፈዋል፡፡
ፊታውራሪ ገበየሁ ገና ወደ ዓድዋ ሲዘምቱ ‹‹ስሸሽ ከኋላዬ ከተመታሁ አሞራ ይብላኝ፤ከፊት ለፊት ስፋለም ከወደቅሁ ግን እሬሳዬን አፅሜን ትውልድ ቦታዬ ውሰዱልኝ›› በማለት ተናዘውም ነበር አሉ፡፡ ከጠላት ጋር በፅናት ሲፋለሙ ስለ ሀገራቸው ነፃነት ዓድዋ ላይ ወደቁ፡፡ በኑዛዜያቸው መሠረትም ከሞቱ ከሰባት ዓመት በኋላ አፅማቸው ወደ ትውልድ አካባቢያቸው አንጎለላ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ተወስዶ እዚያው አረፈ፡፡ ‹‹የዓድዋ ሥላሴን ጠላት አረከሰው፣ ገበየሁ በሞቴ ግባና ቀድሰው›› ተብሎም የተገጠመላቸው ለዚህ ጀግና ነው፡፡

No comments:
Post a Comment