Showing posts with label የፍቅር ት/ቤት. Show all posts
Showing posts with label የፍቅር ት/ቤት. Show all posts

Friday, August 17, 2018

ተመራማሪዎች፡ ትዳር "ጤናን ይጠብቃል"


ትዳር ለጤና ይበጃልImage copyrightGETTY IMAGES

ትዳር ለጤና እንደሚበጅ እና ከፍተኛ የኮሌስትሮል መጠንን የመሰለ ለከባድ የልብ ሕመም የሚያጋልጥ የጤና እክል በሚያጋጥም ወቅት ይህንን ተቋቁሞ የመዳን ዕድልን ከፍ እንደሚያደርግ ተመራማሪዎች ገልፀዋል።
የሚያፈቅሯቸው የትዳር አጋር ያላቸው ሰዎች ራሳቸውን በሚገባ እንዲንከባከቡ ሊያበረታቱዋቸው እንደሚችሉ ያስረዳሉ።

Thursday, August 16, 2018

ከሰዎች ጋር ያለንን ግንኙነት ለማስተካከል የሚረዱ ዘጠኝ ሚስጥሮች


ጥንዶች ሲዝናኑImage copyrightGETTY IMAGES

ጥሩ ጓደኝነትም ይሁን ትዳር፤ የስራ ግንኙነትም ይሁን የፍቅር፤ ከሰዎች ጋር የምንመሰርታቸው ግንኙነቶች በህይወታችን በጣም ጠቃሚዎች ናቸው። ነገር ግን ብዙ ፈተናዎችንም ይዘው ይመጣሉ።
በእነዚህ ግንኙነቶች ውስጥ ሊጠቅሟችሁ የሚችሉ ጥቂት ነጥቦችን ይዘን ቀርበናል።

1. ግጭት ሲፈጠር አይደናገጡ

ሁሌም ቢሆን ግጭትን የምናስተናግድበት መንገድ ወሳኝነት አለው። የተለያዩ ሃሳቦች እና ፍላጎቶች ሁሌም ወደ ግጭት ሊያመሩ ይችላሉ።

Friday, July 6, 2018

መላ በሉኝ ይላሉ ደንበኛችን ታሪኩ ይህ ነዉ


ፍቅራችን የተጀመረዉ 9 ክፍል ተማሪ እያለን ነበር፦አንድ ዩኒቨ ገባን እሳ 3 እኔ ደግሞ 5 ዓመት።
ፍቅራችን የግቢ ተማሪዎችን በሙሉ ያስቀና ነበር,ቁርስ ምሳ እራት ተለያይተን በልተን አናዉቅም፣ሳንተያይ መዋልም ሆነ ማደር አንችልም ቢሆንም ግን ጊዜዉ ደረሰና ተመረቀች።
ከዛ ቃል ተገባባንና 2 ዓመት ልጠብቀኝ ተለያየን።
ሄደች,5 ወር በሃላ ስራ ጀመረች።
ስራ እስክትጀምር ድረስ ኩርስ ምሳ እራት መብላቴን በእያንዳንዱኣ ሰዓት እየደወለች ትጠይቀኝ ነበር እኔም እንደዛዉ።
ከሚገባዉ በላይ አምናታለሁ ታምነኛለች።ሁለታችንም ስለመለየት አስበን አናውቅም፡ቤ/ እንካ ሂደን ሞታችን 1 ቀን እንዲሆን እንፀልይ ነበር።
ስራ ከጀመረች በሃላ ግን ባህሪዋ ተቀየረ
በሆነ ባልሆነዉ መቆጣት ጀመረች
መደወል አቆመች
እኔ ስደዉል እንዴት በዚህ ሰዓት ትደዉላለህ ብላ ትቆጣለች
ብቻ ባህሪዋ ሙሉ በሙሉ ተቀየረ
ከወራት በሃላ እባክህ አትረብሸኝ እኔ የራሴ የምለዉን ህይዎት ጀምሬለሁ /ቱም አንተን 2 አመት መጠበቅ ስለማልችል አለችኝ።
አላመንኩም፦ሄድኩ ከሃላፊዋ ጋር የሞቀ ትዳር መስርታለች
ሰዉየዉ ቆንጆ ቤት እና የቤት መኪና አለዉ ሀብታም ነዉ ወጣት ነዉ፣በመልክ በቁመና በሀብት በሁሉም ነገር ይበልጠኛል።
ቢሆንም ግን አእምሮየ መቀበል አልቻለም፣መማር አቃተኝ፣ነገርካት የራስህ ጉዳይ እኔን አይመለከተኝም ከፈለግህ ገደል ግባ አለችኝ።
አሁኝም አላረፍኩም፡አናገርካት፡ተጠይፋ ሰላም አለችኝ
በመጨረሻ እንዲህ አለችኝ፦ አንተ ለኔ አትመጥንም መጀመሪያ እራስህን ለዉጥ።
ድጋሜ ስሄድ ለፖሊስ አስያዘችኝ፦6 ወር በእስር ቤት አሳለፍኩ፣ት/ ተቃረጠ።በዓቱ ቀጠልኩ፥
ቢሆንም ግን ባህሪየ ተቀየረ,ሴት ካየሁ ያመኛል,ወደኔ ከመጣች እማታለሁ እሳደባለሁ