Monday, July 9, 2018

ኢትዮጵያ የፀጥታው ምክር ቤት በኤርትራ የጣለውን ማዕቀብ እንዲያነሳ ይፋዊ ጥያቄ አቀረበች


ኢትዮጵያ የመንግስታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በኤርትራ የጣለውን ማዕቀብ እንዲያነሳ ይፋዊ ጥያቄ አቀረበች።
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከመንግስታቱ ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር ተወያይተዋል።

በዚህ ወቅትም ተመድ በኤርትራ የጣለውን ማዕቀብ እንዲያነሳ ለዋና ፀሃፊው ይፋዊ ጥያቄያቸውን አቅርበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በኤርትራ በነበራቸው ቆይታ ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር የተለያዩ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል።
በስምምነታቸው ወቅትም በኤርትራ ላይ የተጣሉ ማዕቀቦች እንዲነሱና በአለም አቀፍ የፖለቲካ መድረክ እየደረሰባት ያለው መገለል እንዲያበቃ፥ ኢትዮጵያ ትሰራለች ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ መግለጻቸው ይታወሳል።

የእለቱ ምርጥ ፎቶ




ዶክተር አብይ አህመድን ለመቀበል አደባባይ ከወጡ በርካታ ኤርትራዊያን መካከል

በሰኔ ወር በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ከተከናወኑና ድርጊቶች መካከል ጥቂቶቹ


 
🔯🔯🔯
). የንጉሰ ነገሥት ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ የጀኔቫ ንግግር
ንጉሰ ነገሥት ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ የፋሺስት ኢጣሊያ ወረራን ለዓለም መንግሥታት ማኅበር (League of Nations) ተወካዮች ያሳወቁት 82 ዓመታት በፊት (ሰኔ 23 ቀን 1928 .) ነበር፡፡
...

የኢትዮጵያና የኤርትራ የሰላምና የወዳጅነት ስምምነትን ተፈፃሚ የሚያደርግ ኮሚቴ ስራ ጀመረ


አዲስ አበባ ሰኔ 2/2010 የኢትዮጵያና የኤርትራ የሰላምና የወዳጅነት ስምምነትን ተፈፃሚ የሚያደርግ የጋራ ኮሚቴ ዛሬ ስራ ጀመረ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ትናንት ኤርትራን በጎበኙበት ወቅት በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል በዲፕሎማሲ፣ በትራንስፖርት፣ በድንበር ጉዳዮች፣ በወደብ አጠቃቀም፣ በንግድ እንዲሁም በአፍሪካና ዓለምአቀፍ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ስምምነት ፈርመዋል።

የአባጅፋር ቤተመንግሥት የታደጉኝ ጥሪ

የኢትዮጵያ የቅርሶች ማህደርነት ከሚገለጽባቸው እውነታዎች አንዱ፣ በአገሪቱ ከተሞች በተዘዋወሩ ቁጥር አንድ መገለጫ ቅርስ ይዘው መገኘታቸው ነው፡፡ የአባ ጅፋሯ ጅማ ደግሞ ከእነዚህ ከተሞች አንዷ ናት፡፡ እግር ጥሎት ጅማ የደረሰም የአባ ጅፋር ቤተ መንግሥት ቀዳሚ መዳረሻው ለመሆኑ አያጠራጥርም፡፡ ሆኖም ዛሬ ላይ ነገሮች በተቃራኒው ሆነዋል፡፡ ቀድሞ ሰው የማይለየው የአባጅፋር ቤተ መንግሥት ጊቢ ጭር ብሏል፡፡

በቤቱ
ዙሪያ በገመድ ተከልሎ «ማለፍ ክልክል ነው» የሚል ወረቀት ተንጠልጥሎበታል፡፡ ውብ ገጽታ የነበረው ቤት፤ ካስማዎቹ እየተሰበሩ፣ ግድግዳውም እየረገፈ ነው፡፡ ዕድሜ ጠገቡ የአባ ጅፋር ቤተ መንግሥት የነበረ ገጽታውን አጥቷል፤ በነፋስ ኃይል እንኳን ተገፍቶ የሚወድቅ የሚመስለው ይህ ቤት በተለያዩ እንጨቶች ተደግፏል፤ ከቤትነት ወደ አፈርነት የመቀየር ጉዞውንም የጀመረ ይመስላል፡፡

“የጋሽ ጸጋዬ ግጥሞች ቅኝት”






ከነቢይ መኮንን
.
.
እውነት ለመናገር ስለ ስነግጥም ከመናገር መግጠም ይሻላል። በተለይ እንደ ጋሽ ጸጋዬ ገብረ መድኅን ያለውን የግጥም ነዶው ተከምሮ የማያልቅ ገጣሚን ሥራ መናገር “ሂማሊያን በሁለት ቆራጣ እግር-አሊያም አባይን በጭልፋ” እንደማለት ያለ ነገር ነው። ራሱ ጋሽ ጸጋዬ እንደሚለውም “አንድ ምእመን የሃይማኖቱን ድንጋጌ ከማተቱ ይልቅ፤ በቀጥታ እግዚአብሔርን በእምነት ማገልገሉ እንደሚበልጥበት ሁሉ፤ ባለቅኔም የሥነ-ግጥሞችን የአደራደር ሥርዓትና ድንጋጌ (Form) ከማተቱ ይልቅ ቅኔውን ተቀኝቶ፣ ደርሶ፣ ፍሬ-ሃሳቡን (Content) ማበርከቱ ይበልጥበታል።”

አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ዛሬ አዲስ አበባ ይገባሉ

ሓምሌ 02፣2010
ከኢትዮ ኤርትራ ስምምነት በኋላ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጋር ለመምከር ዛሬ አዲስ አበባ ይገባሉ፡
ጉሬዝ ከ20 ዓመት በኃላ ሁለቱ አገራት ሰላም ማውረዳቸውና ከስምምነት መድረሳቸውን ተከትሎ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እገዛ ለማድረግ መዘጋጀቱን አስታውቀው ነበር፡፡
ሮይተርስ ከኢትዮጵያ የውስጥ ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው  ዋና ፀሀፊውና ጠቅላይ ሚኒስትር ዛሬ ተገናኝተው ይወያያሉ፡፡

በመስቀል አደባባይ ፍንዳታ በተጠረጠሩ ታሳሪዎች ላይ የ11 ቀናት ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ተፈቀደ

ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ወደ ሥልጣን በመጡ በአጭር ጊዜ ውስጥ ላስመዘገቡት ለውጥ የምስጋናና የድጋፍ ሰልፍ ለማድረግ መስቀል አደባባይ በወጡ ሰልፈኞች ላይ በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳን ጨምሮ ሌሎች ኃላፊነታቸውን ባለመወጣት የተጠረጠሩ ታሳሪዎች ላይ ፍርድ ቤት የ11 ቀን የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ፈቀደ፡፡
ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ለፍርድ ቤቱ በሰጡት አስተያየት ‹‹ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ ጥፋተኛ እንዳልሆንኩ ሲያውቁ ይቅርታ ይጠይቁኛል፤›› ሲሉም ተናግረዋል፡፡
ፍርድ ቤቱ ለሐምሌ 13 ቀን 2010 ዓ.ም. ቀጥሯል፡፡