የኢትዮጵያ የቅርሶች ማህደርነት ከሚገለጽባቸው እውነታዎች
አንዱ፣ በአገሪቱ
ከተሞች በተዘዋወሩ
ቁጥር አንድ መገለጫ ቅርስ ይዘው መገኘታቸው ነው፡፡ የአባ ጅፋሯ ጅማ ደግሞ ከእነዚህ ከተሞች አንዷ ናት፡፡ እግር ጥሎት ጅማ የደረሰም የአባ ጅፋር ቤተ መንግሥት ቀዳሚ መዳረሻው ለመሆኑ አያጠራጥርም፡፡ ሆኖም ዛሬ ላይ ነገሮች በተቃራኒው ሆነዋል፡፡ ቀድሞ ሰው የማይለየው የአባጅፋር ቤተ መንግሥት ጊቢ ጭር ብሏል፡፡
በቤቱ ዙሪያ በገመድ ተከልሎ «ማለፍ ክልክል ነው» የሚል ወረቀት ተንጠልጥሎበታል፡፡ ያ ውብ ገጽታ የነበረው ቤት፤ ካስማዎቹ እየተሰበሩ፣ ግድግዳውም እየረገፈ ነው፡፡ ዕድሜ ጠገቡ የአባ ጅፋር ቤተ መንግሥት የነበረ ገጽታውን አጥቷል፤ በነፋስ ኃይል እንኳን ተገፍቶ የሚወድቅ የሚመስለው ይህ ቤት በተለያዩ እንጨቶች ተደግፏል፤ ከቤትነት ወደ አፈርነት የመቀየር ጉዞውንም የጀመረ ይመስላል፡፡
እልህና ቁጭት የሚነበብባቸው የጅማ ከተማ ነዋሪዎችም በዚህ ቅርስ በዚህ ደረጃ መገኘት እጅጉን ማዘናቸውን ይናገራሉ፡፡ ቅርሱን ለመታደግ የሚችሉትን ሁሉ ቢጥሩም ሥራው ከእነርሱ አቅም በላይ በመሆኑ ለሚመለከተው አካል በማሳወቅ ቅርሱን የሚታደጉበትን ምላሽ በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውንም ይገልጻሉ፡፡ የሚመለከተው አካልም የከተማዋ ብቻ ሳይሆን የአገር ቅርስ የሆነውን የአባ ጅፋር ቤተመንግሥት ከመፍረስ አደጋ እንዲታደገው ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡
«አሁን ላይ ቤተ መንግሥቱ በፅኑ ታሞ አልጋ ላይ እንደተኛ ህመምተኛ፣ ያውም ለሞት ከጫፍ የደረሰና በከፍተኛ ክትትል ስር እንዳለ ታማሚ ነው» የሚሉት የከተማዋ ነዋሪና የቅርስ ተቆርቋሪ የሆኑት አቶ አብዱልከሪም አባገሮ ናቸው፡፡ እርሳቸው እንደሚሉት፤ አንድ ሰው በጤንነቱ ሳለ ተገቢውን አገልግሎት ሲሰጥ ቢኖርም በጊዜው መድከሙ ወይም መታመሙ አይቀርም፡፡ ይህ ሲሆን ደግሞ ከእርሱና በእርሱ ሲገለገሉ የነበሩ አካላት ሁሉ ለዚያ ሰው ፈውስ ተገቢውን ህክምና እንዲያገኝ መስራት ይጠበቅባቸዋል፡፡ የአባ ጅፋር ቤተ መንግሥትም ተመሳሳይ ችግር ገጥሞታል፡፡
ምክንያቱም ቤተ መንግሥቱ በጅማ ከተማ ይገኝ እንጂ ሀብትነቱም ሆነ ጥቅሙ የአገር ነው፡፡ ሆኖም አሁን ላይ ቤተ መንግሥቱ ከፍተኛ አደጋ ውስጥ ገብቷል፡፡ አደጋውም እጅጉን የከፋ እንደመሆኑ በጽኑ የህክምና ክትትል ስር ያለ ሰው ተገቢውን የባለሙያ ክትትል ካላገኘ እንደሚሞት ሁሉ፤ ይህ ቤተ መንግሥትም በከፍተኛ አደጋ ውስጥ ያለ እንደመሆኑ አጥሮ ለጎብኚዎች ዝግ ማድረግ መፍትሄ ስለማይሆን በተገቢው ባለሙያ ተገቢው ጥገና ሊደረግለት ያስፈልጋል፡፡
አቶ አብዱልከሪም እንደሚሉት፤ የሰው ልጅ ከሞተ ሕይወቱ መመለስ እንደማይችል ሁሉ ይህ ቤትም አንዴ ከፈረሰ በኋላ መልሶ መተካት አይቻልም፡፡ ይህ ቅርስ ደግሞ የቀደሙት አባቶች አኑረው ያለፉት አሻራ ነው፡፡ ይህን አሻራ ከትውልድ ተረክቦና ጠብቆ የማቆየት ድርሻ ደግሞ አሁን ያለው ትውልድ ነው፡፡ ሆኖም አሁን ባለበት ደረጃ ቅርሱ እየፈረሰ ብቻ ሳይሆን፤ ትውልዱም የተረከበውን የታሪክ አደራ ተሸካሚ መሆኑ ላይ ጥያቄ የሚያስነሳ ነው፡፡ በመሆኑም የታሪክ ተወቃሽ ላለመሆን ባለታሪኮች የሰሩትን ይሄን ቅርስ መጠገንና ጠብቆ ማቆየት ተገቢ ነው፡፡ በመሆኑም ይሄን ቅርስ የከተማዋ ዓርማ ብቻ ሳይሆን የአገር ሀብት እንደመሆኑ የሚመለከተው አካል ተገቢው ትኩረት ሊሰጠውና ሊታደገው ይገባል ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የጅማ ከተማ ከንቲባ አቶ መኪዩ መሐመድ፣ የነዋሪዎቹን ሃሳብ ይጋራሉ፡፡ እርሳቸው እንደሚሉት፤ በአባ ጅፋር ቤተመንግሥት ላይ የተደቀነው ችግር ዛሬ የጀመረ ሳይሆን የቆየ ነው፡፡ ቅርሱን ለመጠገን ደግሞ ከተማ አስተዳደሩ የሚችለውን ሁሉ እያደረገ ቢሆንም ከአስተዳደሩ አቅም በላይ ሆኗል፡፡ የችግሩን መባባስ ተከትሎም ባለፈው ዓመት ለክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አሳውቀዋል፡፡ በቢሮው ደረጃ የተደረገው ጥረትም ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ ምክንያቱም ቅርሱ በዘርፉ ሙያና ልምድ ባላቸው እንጂ በሰፈር ባለሙያዎች የሚከናወን ከሆነ የባሰ አደጋ ላይ የሚወድቅ መሆኑ በ1997 ዓ.ም በተደረገ የጥገና ሥራ ታይቷል፡፡
ይሄን በመገንዘብም የክልሉ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጉዳዩን ለፌዴራል አሳልፏል፡፡ ይሁን እንጂ በፌዴራል የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር መወሰድ የሚገባው እርምጃ የተጓተተ በመሆኑ ቤቱ የበለጠ ለአደጋ እየተጋለጠ ይገኛል፡፡ እናም ይህ የከተማው መለያ ብቻ ሳይሆን የአገር ሀብት የሆነው ቅርስ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ተገቢውን ትኩረት ሊሰጡት ይገባል፡፡
በቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን የቅርስ ጥበቃና እንክብካቤ ዳይሬክተር አቶ ኃይሉ ዘለቀ፣ በጉዳዩ ዙሪያ በሰጡት አስተያየት፤ የአባ ጅፋር ቤተመንግሥት እስካሁን በክልል ስር ሲተዳደር የቆየ ነው፡፡ ለማስጠገን በሚልም ጨረታ አውጥቶ ሰጥቶ ስለነበረ፤ ይህ ጨረታ ተቋርጦ ውክልናውን ለባለሥልጣኑ መስጠት ነበረበት፡፡ ይህ እስኪሆንም ኤጀንሲው ዝም ብሎ አልተቀመጠም፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አማካኝነት ጥናት እያስጠና ሲሆን፤ ጥናቱ እስኪጠናቀቅም ከክልሉ ጋር በመሆን መለስተኛ የጥበቃና እንክብካቤ ሥራ እያከናወነ ይገኛል፡፡
እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ፤ ባለሥልጣኑ ሥራውን ለማከናወን የሚያስችሉ አሠራሮችን ለመከተል እንጂ ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት ዘግይቷል የሚያስብል ሂደት አልወሰደም፡፡ ሥራውን ለማከናወን የሚያስችለው ጥናትም መስከረም አጋማሽ ላይ ስለሚጠናቀቅ በመንግሥት ከሚበጀተው ፋይናንስ ባለፈ ለጥገና ሥራው የሚውል ፈንድ እየተፈላለገ ነው፡፡ እንደነ ላሊበላ ሁሉ የአባ ጅፋር ቤተመንግሥትም ቅድሚያ የተሰጠው ተግባር በመሆኑ ከመስከረም አጋማሽ በኋላ የዝናቡ ወቅት እንዳበቃ የጥገና ሥራው የሚጀመር ይሆናል፡፡

No comments:
Post a Comment