ድምፃዊ ኤፍሬም ታምሩ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 410/96 እና የተሻሻለውን አዋጀ ቁጥር 872/2007 አንቀጽ (41)ን ተላልፏል ተብሎ፣ የተመሠረተበትን የፍትሐ ብሔር ክስ ማስተባበል ባለመቻሉ ቅጣት ተወሰነበት፡፡
ድምፃዊው የገንዘብ ቅጣት የተወሰነበት በ1977 ዓ.ም. ባሳተመው የካሴት ዘፈን ውስጥ ‹‹የቀይ ዳማ›› ወይም ‹‹የድንገት እንግዳ›› የሚል ርዕስ ያለውን ዘፈን ደራሲ የአቶ ማስረሻ ሽፈራውን ወራሽ ወ/ሮ ቤተልሔም ማስረሻን ሳያስፈቅድ፣ እንደ አዲስ ሙዚቃ በማቀናበር በ2007 ዓ.ም. በድጋሚ አሳትሞ ለሕዝብ አሠራጭቷል የሚለው ክስ በማስረጃ በመረጋገጡ መሆኑን የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ያስረዳል፡፡
ከሳሽ ወ/ሮ ቤተልሔም ለፍርድ ቤቱ ባቀረቡት ክስ እንዳስረዱት፣ አባታቸው አቶ ማስረሻ የ‹‹ቀይ ዳማ›› ዘፈን ብቸኛ ደራሲ ናቸው፡፡ አባታቸው ጥቅምት 19 ቀን 1994 ዓ.ም. አርፈው በማግሥቱ ጥቅምት 20 ቀን 1994 ዓ.ም. ሥርዓተ ቀብራቸው መፈጸሙን፣ እሳቸውም ወራሽ ስለመሆናቸው የአዲስ አበባ ከተማ የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 4239/07 ውሳኔ
ማረጋገጡን ለፍርድ ቤቱ አሳውቀዋል፡፡
የአባታቸውን ድርሰት ያለሳቸው ፈቃድ ድምፃዊው በሙዚቃ አቀናብሮና አሳትሞ በልዩ ልዩ ማኅበራዊ ድረ ገጾችና ኤፍኤም ሬዲዮ ጣቢያዎች በማሠራጨት፣ የጥቅምና የሞራል ጉዳት እንዳደረሰባቸው ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም ድምፃዊው አዋጆቹን በመተላለፍ ያሳተመው ቅጅ እንዲታገድ፣ ፈቃድ ቢጠይቃቸው ኖሮ ሊያገኙ ይችሉ የነበረውን 30,000 ብር፣ እንዲሁም ለደረሰባቸው የሞራል ጉዳት ካሳ ደግሞ 140,000 ብር እንዲከፍላቸው እንዲወሰንላቸው ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል፡፡
No comments:
Post a Comment