
ከነቢይ መኮንን
.
.
እውነት ለመናገር ስለ ስነግጥም ከመናገር መግጠም ይሻላል። በተለይ እንደ ጋሽ ጸጋዬ ገብረ
መድኅን ያለውን የግጥም ነዶው ተከምሮ የማያልቅ ገጣሚን ሥራ መናገር “ሂማሊያን በሁለት ቆራጣ እግር-አሊያም አባይን በጭልፋ”
እንደማለት ያለ ነገር ነው። ራሱ ጋሽ ጸጋዬ እንደሚለውም “አንድ ምእመን የሃይማኖቱን ድንጋጌ ከማተቱ ይልቅ፤ በቀጥታ
እግዚአብሔርን በእምነት ማገልገሉ እንደሚበልጥበት ሁሉ፤ ባለቅኔም የሥነ-ግጥሞችን የአደራደር ሥርዓትና ድንጋጌ (Form)
ከማተቱ ይልቅ ቅኔውን ተቀኝቶ፣ ደርሶ፣ ፍሬ-ሃሳቡን (Content) ማበርከቱ ይበልጥበታል።”