Showing posts with label አቦል መረጃ. Show all posts
Showing posts with label አቦል መረጃ. Show all posts

Friday, August 17, 2018

የሜክሲኮ ተማሪዎች ወሲባዊ ትንኮሳን የሚከላከል ካፖርት ፈለሰፉ



የካፖርቱ እጀታ ከነዛሪ ኤሌክትረክ የተሰራ ነውImage copyrightCONACYT
አጭር የምስል መግለጫየካፖርቱ እጀታ ከነዛሪ ኤሌክትረክ የተሰራ ነው

አራት ሜክሲኳውያን ተማሪዎች ከጾታዊ ጥቃት የሚከላከል ካፖርት ፈልስፈዋል። የካፖርቱ እጀታ የተሰራው ከሚነዝር ኤሌክትሪክ ሲሆን፤ ጥቃት የሚሰነዝር ሰው ካፖርቱን የለበሰን ሰው ክንድ ሲይዝ እንዲነዝረው ያደርጋል።

Thursday, August 16, 2018

የ"ይቻላል" መንፈስ የሰፈነበት የአዲስ አበባው ቴድኤክስ የንግግር መድረክ

የቴዴክስ አዲስ ተሳታፊዎች
ልጅ ሳለ ሰዎች በስልክ ሲነጋገሩ ያያል። 'እንዴት ድምጽ በቀጭን ሽቦ ይተላለፋል?' ሲል በጠያቂ አእምሮው ያሰላስላል። አውጥቶ አውርዶም ስልክ ለመፈልሰፍ ይወስናል።
ያስፈልጉኛል ያላቸውን እቃዎች ከአካባቢው መሰብሰብ ጀመረ። ጣሳን ለድምጽ መሳቢያነት ተጠቅሞ ከጭቃ የተሰራ የስልክ እጀታ ሠራ።
ስልክ የመጀመሪያ የፈጠራ ሙከራው አይደለም። ዘወትር አዳዲስ ነገር ስለመፈልሰፍ ከማሰብ ወደ ኋላ አይልም። እስራኤል ቤለማ ይህ ባህሪው የኢንጂነርነት ሙያን ለመቀላለል እንዳበቃው የተናገረው ከቴድኤክስ አዲስ መድረኮች በአንዱ ነበር።

Monday, July 30, 2018

‹‹ከእኔ ክስና እስራት በስተጀርባ በመንግሥት ውስጥ ጡንቻቸው የጠነከረ ማፊያዎች ነበሩ››



አቶ መላኩ ፈንታ፣ የቀድሞ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር


የዛሬው የቆይታ አምድ እንግዳ አቶ መላኩ ፈንታ ናቸው፡፡ 50 ዓመት ጎልማሳው አቶ መላኩ 1981 .. ጀምሮ እስከ 2005 ድረስ በተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ውስጥ ከጀማሪ ኤክስፐርትነት እስከ ሚኒስትርነት ባሉ ኃላፊነቶች ከመሥራታቸው በተጨማሪ፣ በሠሩባቸውና በመሯቸው ተቋማት ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ለውጥ በማምጣት የተመሠከረላቸው ናቸው፡፡ በተለይ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣንን በሚኒስትር ማዕረግ በዋና ዳይሬክተርነት መምራታቸው ይታወሳል፡፡ 2005 .. ግንቦት ወር ጀምሮ በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረውና ክስ ተመሥርቶባቸው ለአምስት ዓመታት እስከ ግንቦት ወር 2010 .. ድረስ ታስረው ቆይተዋል፡፡ በቂ መረጃ ሳይሰበስብ ከሁለት ወይም ከሦስት ክሶች መብለጥ የሌለባቸውን ክሶች አብዝቶ በመክሰስ ዜጎችን ለእስር መዳረግ ተገቢ አለመሆኑን፣ ለፖለቲካ ፍጆታ ተብሎ ዜጎች ያለ ወንጀላቸው በወንጀል ተፈርጀው መታሰራቸው የፖለቲካ ምኅዳሩን ከማጥበብና ሰላምን ከማደፍረስ የዘለለ ሚና እንደሌለው መንግሥት ገልጾ፣ የበርካታ እስረኞች ክስ እንዲቋረጥና በይቅርታ እንዲፈቱ ሲያደርግ ለመጨረሻ የቅጣት ውሳኔ የተቀጠሩት አቶ መላኩም ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር ተፈትተዋል፡፡ ባለትዳርና የአራት ልጆች አባት የሆኑትን አቶ መላኩ በትምህርት፣ በሥራ፣ በእስር ስላሳለፏቸው ጊዜያትና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ከሪፖርተር ጋዜጣ ጋር ያደረጉትን እንሆ።

Thursday, July 26, 2018

እጅግ አሳዛኝ እና አስደንጋጭ ዜና

የሕዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ስመኘው በቀለ ዛሬ (ሐሙስ ሐምሌ 19 ቀን 2010 ዓ.ም.) ጠዋት አዲስ አበባ አብዮት አደባባይ በመኪናቸዉ ዉስጥ ሞተዉ ተገኙ፡፡

Monday, July 23, 2018

ኢትዮጵያ እና ኤርትራ የወዳጅነት ጨዋታ ሊያደርጉ ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከኤርትራ አቻው ጋር በነሐሴ ወር አጋማሽ አስመራ ላይ የወዳጅነት ጨዋታ ሊያደርግ ነው።የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሁለቱን ሀገራት ወንድማማችነት ለማጠናከር አስመራ ከተማ ላይ የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ ባሳለፍነው ሳምንት ደብዳቤ መላኩ ይታወሳል።

በ50 የዓለማችን አገራት የኤችአይቪ ስርጭት ጨምሯል


50 የተለያዩ የዓለማችን አገራት የኤችአይቪ ኤድስ ስርጭት እየጨመረ መምጣቱንና በቫይረሱ እየተጠቁ ካሉት ሰዎች ግማሽ ያህሉ የመድሃኒትና የህክምና አገልግሎቶችን እያገኙ እንዳልሆነ ዩኤንኤድስ የተባለው አለማቀፍ ተቋም ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል፡፡

ድምፃዊ ኤፍሬም ታምሩ የቅጅ መብት ሕግ ጥሷል ተብሎ የፍትሐ ብሔር ቅጣት ተወሰነበት


ድምፃዊ ኤፍሬም ታምሩ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 410/96 እና የተሻሻለውን አዋጀ ቁጥር 872/2007 አንቀጽ (41) ተላልፏል ተብሎ፣ የተመሠረተበትን የፍትሐ ብሔር ክስ ማስተባበል ባለመቻሉ ቅጣት ተወሰነበት፡፡

Sunday, July 22, 2018

570 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በህገ-ወጥ መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ጅግጅጋ ሲጓጓዝ ተያዘ


570 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በህገ-ወጥ መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ጅግጅጋ ሲጓጓዝ በቁጥጥር ስር መዋሉን የምስራቅ ሸዋ ዞን ፖሊስ አስታወቀ።

ባለፉት ቀናት በተከናወነ ኦፕሬሽን 10 ሚሊየን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ መያዙን ፖሊስ ገለፀ

ጥናትን መሰረት በማድረግ ባለፉት ጥቂት ቀናት በአዲስ አበባ እና ከአዲስ አበባ ውጪ በተከናወነ ኦፕሬሽን በህገወጥ መንገድ የተያዘ 10 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ መያዙን የፌደራል ፖሊስ ገለፀ።

Saturday, July 14, 2018

ዶክተር አብይ አህመድ በ BBC አልጀዚራና ሌሎች አለም አቀፍ ሚዲያዎች እይታ

የዶክተር አብይ የመቶ ቀናት መቶ ሰበር ዜናዎች


1. መጋቢት 24 - ኢትዮጵያዊነት፣ ፍትህ፣ እኩልነት የታወጀበት የበአለ-ሲመት ንግግር
2.
መጋቢት 25 - ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ህብረት ጋር የጀመረቻቸውን ስራዎች እንደምትቀጥል የተገለፀበት
3.
መጋቢት26 - ከፕ/ አልሲ ጋር በስልክ አወ\ የደስታ መግለጫ ተለዋወጡ
4.
መጋቢት 28 - እስረኞች የተፈቱበትና ማዕከላዊ በይፋ የተዘጋበት
5.
መጋቢት 29 - የመጀመሪያው ህዝባዊ መድረክ በጅግጅጋ
6.
ሚያዚያ 02 - የኬኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርን በፅ/ቤታቸው ተቀብለው ማነጋገር
7.
ሚያዚያ 03 - ህዝባዊ መድረክ በአምቦ

ለኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በብሔራዊ ቤተ መንግስት የተዘጋጀ ዝግጅት ላይ የተደረገ የስጦታ ፕሮግራም


የከተማ አስተዳደሩ ዋና ኦዲተር ትልልቅ ጉድለቶችን ለከተማው ምክር ቤት አቅርቧል፡፡


1. ከደንብና መመሪያ ውጭ የተፈጸመ ግዥ……….…112 ሚሊየን ብር በላይ
2. በወቅቱ ያልተሰበሰበ…………..............….329 ሚሊዬን ብር በላይ

3. ጥሬ እቃ ተሰጥቶ ምላሽ ያልተደረገ……......41 ሚሊዬን ብር በላይ
4.
ለማን እንደሚከፈል የማይታወቅ ተከፋይ ሂሳብ….123 ሚሊዬን ብር በላይ


ፈረስ ከእነ ጋሻና ጦር ስጦታ


የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ ፈረስ ከእነ ጋሻና ጦር ስጦታ ተበረከተላቸው።



Monday, July 9, 2018

ኢትዮጵያ የፀጥታው ምክር ቤት በኤርትራ የጣለውን ማዕቀብ እንዲያነሳ ይፋዊ ጥያቄ አቀረበች


ኢትዮጵያ የመንግስታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በኤርትራ የጣለውን ማዕቀብ እንዲያነሳ ይፋዊ ጥያቄ አቀረበች።
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከመንግስታቱ ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር ተወያይተዋል።

በዚህ ወቅትም ተመድ በኤርትራ የጣለውን ማዕቀብ እንዲያነሳ ለዋና ፀሃፊው ይፋዊ ጥያቄያቸውን አቅርበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በኤርትራ በነበራቸው ቆይታ ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር የተለያዩ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል።
በስምምነታቸው ወቅትም በኤርትራ ላይ የተጣሉ ማዕቀቦች እንዲነሱና በአለም አቀፍ የፖለቲካ መድረክ እየደረሰባት ያለው መገለል እንዲያበቃ፥ ኢትዮጵያ ትሰራለች ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ መግለጻቸው ይታወሳል።