Friday, August 17, 2018

የሜክሲኮ ተማሪዎች ወሲባዊ ትንኮሳን የሚከላከል ካፖርት ፈለሰፉ



የካፖርቱ እጀታ ከነዛሪ ኤሌክትረክ የተሰራ ነውImage copyrightCONACYT
አጭር የምስል መግለጫየካፖርቱ እጀታ ከነዛሪ ኤሌክትረክ የተሰራ ነው

አራት ሜክሲኳውያን ተማሪዎች ከጾታዊ ጥቃት የሚከላከል ካፖርት ፈልስፈዋል። የካፖርቱ እጀታ የተሰራው ከሚነዝር ኤሌክትሪክ ሲሆን፤ ጥቃት የሚሰነዝር ሰው ካፖርቱን የለበሰን ሰው ክንድ ሲይዝ እንዲነዝረው ያደርጋል።
ተማሪዎቹ ካፖርቱን የፈለሰፉት ሀገራቸው ውስጥ የተንሰራፋውን ወሲባዊ ትንኮሳ ለመከላከል ሲሆን፤ "ውሜን ዌረብል"ወይም "እንስቶች የሚለብሱት" የተሰኘ ስያሜ ተሰጥቶታል።
ከአራቱ ተማሪዎች ሁለቱ አናይድ ፓራ ኮሬዝ እና ኤስቴላ ጎሜዝ የሜካትሮኒክስ ኢንጅነሪንግ ተማሪዎች ናቸው። የሮቦቲክስ ተማሪዋ ግዌን ፓርክ እንዲሁም የህግ ተማሪ ጉዋዱልፔ ማርቲኔዝም ተሳትፈዋል።


አራቱ የካፖርቱ ፈልሳፊዎችImage copyrightITESM
አጭር የምስል መግለጫአራቱ የካፖርቱ ፈልሳፊዎች

ፈልሳፊዎቹ የፈጠራ ኃሳቡ ብልጭ ያለላቸው ለአንድ የትምህርት ክፍለ ጊዜ ፕሮጀክት ሲያውጠነጥኑ ነበር። አናይድ ፓራ "ብዙ ሴት ጓደኞቻችን የሀይል ጥቃት ይደርስባቸዋል። ጾታን መሰረት ስላደረገ ጥቃት ጥናት ከሰራን በኃላ ካፖርቱን ለመስራት ወሰንን" ትላለች።
በሚኖሩበት የሜክሲኮዋ ፑቤላ ግዛት በየቀኑ ወሲባዊ ትንኮሳ ይደርሳል።
ካፖርቱ የተሰራው ከጥጥ ሲሆን፤ ዘጠኝ ቮልት የኤሌክትሪክ ሀይል የሚያመነጭ ባትሪ ውስጡ ተቀብሯል። የኤሌክትሪክ ገመዱ በካፖርቱ ውስጥ ለውስጥ ይዘዋወራል። ካፖርቱ ኤሌክትሪክ እንዲያመነጭ መዝጊያው (ዚፕ) ላይ ማብሪያና ማጥፊያ ተገጥሞለታል።


ካፖርቱ የሚሰራው ቀልፉን በመጫን ነውImage copyrightCONACYT
አጭር የምስል መግለጫካፖርቱ የሚሰራው ቀልፉን በመጫን ነው

አንድ ሰው ካፓርቱን የለበሰ ሰውን ለማጥቃት አስቦ የተጠቂውን ክንድ ቢይዝ የኤሌክትሪክ ንዝረት ይከተላል። አጥቂው በኤሌክትሪክ ንዝረቱ ሲንዘፈዘፍ ተጠቂው ከአካባቢው ርቆ ለመሸሽ ጊዜ ያገኛል።
የህግ ተማሪው ጉዋዱልፔ ማርቲኔዝ፤ ካፖርቱን ጥቅም ላይ ማዋል የህግ ጥያቄ እንደማያስነሳ ሲያስረግጥ "አላማው ራስን መከላከል ብቻ ነው" በማለት ነው።
ካፖርቱ የሚያመነጨው የኤሌክትሪክ ንዝረት ለህይወት ስለማያሰጋ እንደ መሳሪያ ሊቆጠር እንደማይቻልም ያስረዳል።
የካፖርቱን ንድፈ ሀሳብ የሚያሳይ የሙከታ ስራ (ፕሮቶታይፕ) ለማጠናቀቅ ሶስት ወር ወስዶባቸወሰል። በቀጣይ የኤሌክትሪክ ኃይሉን ከካፖርቱ እጀታ በዘለለ በሌሎች የካፖርቱ ክፍሎችም የመግጠም እቅድ አላቸው።
ተማሪዎቹ ተመሳሳይ መንገድ በመጠቀም ነዛሪ ካናቴራ፣ ቀሚስና ሱሪም ለመስራት አስበዋል። ካፖርቱ ገበያ ላይ ከዋለ 50 ዶላር የሚሸጥ ይሆናል።

No comments:

Post a Comment