Saturday, July 14, 2018
Monday, July 9, 2018
ኢትዮጵያ የፀጥታው ምክር ቤት በኤርትራ የጣለውን ማዕቀብ እንዲያነሳ ይፋዊ ጥያቄ አቀረበች
ኢትዮጵያ የመንግስታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በኤርትራ የጣለውን ማዕቀብ እንዲያነሳ ይፋዊ ጥያቄ አቀረበች።
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከመንግስታቱ ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር ተወያይተዋል።
በዚህ ወቅትም ተመድ በኤርትራ የጣለውን ማዕቀብ እንዲያነሳ ለዋና ፀሃፊው ይፋዊ ጥያቄያቸውን አቅርበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በኤርትራ በነበራቸው ቆይታ ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር የተለያዩ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል።
በስምምነታቸው ወቅትም በኤርትራ ላይ የተጣሉ ማዕቀቦች እንዲነሱና በአለም አቀፍ የፖለቲካ መድረክ እየደረሰባት ያለው መገለል እንዲያበቃ፥ ኢትዮጵያ ትሰራለች ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ መግለጻቸው ይታወሳል።
በሰኔ ወር በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ከተከናወኑና ድርጊቶች መካከል ጥቂቶቹ
፩). የንጉሰ ነገሥት ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ የጀኔቫ ንግግር
ንጉሰ ነገሥት ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ የፋሺስት ኢጣሊያ ወረራን ለዓለም መንግሥታት ማኅበር (League of Nations) ተወካዮች ያሳወቁት ከ82 ዓመታት በፊት (ሰኔ 23 ቀን 1928 ዓ.ም) ነበር፡፡
...
የአባጅፋር ቤተመንግሥት የታደጉኝ ጥሪ
የኢትዮጵያ የቅርሶች ማህደርነት ከሚገለጽባቸው እውነታዎች
አንዱ፣ በአገሪቱ
ከተሞች በተዘዋወሩ
ቁጥር አንድ መገለጫ ቅርስ ይዘው መገኘታቸው ነው፡፡ የአባ ጅፋሯ ጅማ ደግሞ ከእነዚህ ከተሞች አንዷ ናት፡፡ እግር ጥሎት ጅማ የደረሰም የአባ ጅፋር ቤተ መንግሥት ቀዳሚ መዳረሻው ለመሆኑ አያጠራጥርም፡፡ ሆኖም ዛሬ ላይ ነገሮች በተቃራኒው ሆነዋል፡፡ ቀድሞ ሰው የማይለየው የአባጅፋር ቤተ መንግሥት ጊቢ ጭር ብሏል፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)






