Sunday, July 22, 2018

ሰማይና ምድር በምስክርነት


አንድ ነጋዴ የተለያዩ እቃዎችን በአጋሰሶቹ ጭኖ በጉዞ ላይ እንዳለ ሶስት ቀማኞች ከመንገድ ጠብቀው እቃዎቹንና ብሩን ይዘርፉታል፡፡ነጋዴውም በፍርድ አሰጣጥ ችሎታቸውና በዘዴኝነታቸው ታዋቂ ወደነበሩት ፊታውራሪ ሃብተገወርጊስ ወይም አባ መላ ችሎት በመቅረብ በደሉን ያሰማል፡፡

የተጠረጠሩት ተይዘው ሲመረመሩም ወንጀላቸውን በመካዳቸው ተበዳይ ነኝ ባይ ምስክሮቹን እንዲያመጣ ይየቃል፡፡ ተበዳዩ ግን ምስክሬ ሰማይና ምድር ነው በማለት መልስ ይሰጣል፡፡ በዚህ መሰረትም ፍታውራሪ ሃብተጊወርጊስ ሁለቱን ቀማኞችና ነጋዴውን ከአንድ እመኝ ጋር በማድረግ ንብረቱ ተዘረፈ ወደተባለበት ቦታ ሄደው እንዲመሳከሩ ትዕዛዝ ሰጥተው ይልኳቸዋል፡፡
ከቀማኞቹ አንዱን ግን አጠገባቸው እንዲቆይ አደረጉ፡፡ትቂት ከቆዩ በኋላ አጠገባቸው ያለውን ጠየቁት፡፡
እንዲመሳከሩ የላክኋቸው ሰዎች እስካሁን ከዘረፋችሁበት ቦታ ይደርሱ ይሆን አሉት፡፡ ችሎቱ አጠገብ የተቀመጠው ቀማኛም ድንግጥ ይልና አይደርሱም ጌታዬ ትንሽ ይቀራቸዋል ብሎ ይመልስላቸዋል፡፡
አባመላም የፈለጉትን ነገር ስላገኙ እውነትም ሰማይና ምድር መስክረዋል ሂድና ሰዎችን መልሳቸው በማለት ፈረሰኛ ልከው ቀማኞችን በማስመጣት የነጋዴውን ሃብት አስመለሱለት፡፡ ጥፋተኞችንም ወደ እስር ቤት ላኳቸው፡፡

(ፍታውራሪ ሃብተጊወርጊስ ወይም አባመላ መፅሃፍ የተወሰደ)

No comments:

Post a Comment