Saturday, August 18, 2018

ነሐሴ 12 – የሦስቱ ታላላቅ የልደት ቀን

ነሐሴ 12 ታሪካዊ ቀን ናት፤ በዚች ቀን በኢትዮጵያ ታሪክ ጉልህ ስፍራ ያላቸው ግለሰቦች ተወልደዋልና፡፡ በተለያዩ ዓመታት ቢሆንም ንጉሰ ነገሥት ዳግማዊ አፄ ምኒልክ፣ እቴጌ ጣይቱ ብጡል እና ፊታውራሪ ገበየሁ የተወለዱት ነሐሴ 12 ቀን ነው፡፡

Friday, August 17, 2018

ስለ ኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ምን ያህል ያውቃሉ?


የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፍወርቂን የሚያሳይ ምስልImage copyrightGETTY IMAGES
አጭር የምስል መግለጫየኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፍወርቂ

ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት የትኛውም ቃለ መጠይቅ ምንም አይነት ነገር ስለ ግለ ህይወታቸው አውርተው የማያውቁት የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ፤ ጥቂት የሚባሉ ሰዎች ብቻ ስለ ግል ህይወታቸው ያውቃሉ።

ተመራማሪዎች፡ ትዳር "ጤናን ይጠብቃል"


ትዳር ለጤና ይበጃልImage copyrightGETTY IMAGES

ትዳር ለጤና እንደሚበጅ እና ከፍተኛ የኮሌስትሮል መጠንን የመሰለ ለከባድ የልብ ሕመም የሚያጋልጥ የጤና እክል በሚያጋጥም ወቅት ይህንን ተቋቁሞ የመዳን ዕድልን ከፍ እንደሚያደርግ ተመራማሪዎች ገልፀዋል።
የሚያፈቅሯቸው የትዳር አጋር ያላቸው ሰዎች ራሳቸውን በሚገባ እንዲንከባከቡ ሊያበረታቱዋቸው እንደሚችሉ ያስረዳሉ።

የሜክሲኮ ተማሪዎች ወሲባዊ ትንኮሳን የሚከላከል ካፖርት ፈለሰፉ



የካፖርቱ እጀታ ከነዛሪ ኤሌክትረክ የተሰራ ነውImage copyrightCONACYT
አጭር የምስል መግለጫየካፖርቱ እጀታ ከነዛሪ ኤሌክትረክ የተሰራ ነው

አራት ሜክሲኳውያን ተማሪዎች ከጾታዊ ጥቃት የሚከላከል ካፖርት ፈልስፈዋል። የካፖርቱ እጀታ የተሰራው ከሚነዝር ኤሌክትሪክ ሲሆን፤ ጥቃት የሚሰነዝር ሰው ካፖርቱን የለበሰን ሰው ክንድ ሲይዝ እንዲነዝረው ያደርጋል።

Thursday, August 16, 2018

የገበያ ዳኛ እና መርካቶ


ዛሬ ላይ ከኒዮርክና ብራስልስ ቀጥላ የበርካታ ዓለም አቀፍ ዲፕሎማቶች መቀመጫ የሃገረ ኢትዮጵያ ርዕሰ መዲና ብቻ ሳትሆን የኢኮኖሚውም ማዕከል ነች አዲስ አበባ፡፡ ከተመሰረተችበት እለት አንስቶ በርካታ ታሪካዊ ሂደቶችን አሳልፋለች፡፡ ገና በልጅነቷ ወቅት ከነበሯት አይረሴ ትዝታዎች መሃከል የግብይት እንቅስቃሴዋና የገበያ ዳኛ አንዱ ነው፡፡
በዛሬ መሰናዷችንም ይሄንን ጉዞዋን ልናስቃኛችሁ ወደናል፡፡ አብረራችሁን ቆዩ፡፡

የ"ይቻላል" መንፈስ የሰፈነበት የአዲስ አበባው ቴድኤክስ የንግግር መድረክ

የቴዴክስ አዲስ ተሳታፊዎች
ልጅ ሳለ ሰዎች በስልክ ሲነጋገሩ ያያል። 'እንዴት ድምጽ በቀጭን ሽቦ ይተላለፋል?' ሲል በጠያቂ አእምሮው ያሰላስላል። አውጥቶ አውርዶም ስልክ ለመፈልሰፍ ይወስናል።
ያስፈልጉኛል ያላቸውን እቃዎች ከአካባቢው መሰብሰብ ጀመረ። ጣሳን ለድምጽ መሳቢያነት ተጠቅሞ ከጭቃ የተሰራ የስልክ እጀታ ሠራ።
ስልክ የመጀመሪያ የፈጠራ ሙከራው አይደለም። ዘወትር አዳዲስ ነገር ስለመፈልሰፍ ከማሰብ ወደ ኋላ አይልም። እስራኤል ቤለማ ይህ ባህሪው የኢንጂነርነት ሙያን ለመቀላለል እንዳበቃው የተናገረው ከቴድኤክስ አዲስ መድረኮች በአንዱ ነበር።

ከሰዎች ጋር ያለንን ግንኙነት ለማስተካከል የሚረዱ ዘጠኝ ሚስጥሮች


ጥንዶች ሲዝናኑImage copyrightGETTY IMAGES

ጥሩ ጓደኝነትም ይሁን ትዳር፤ የስራ ግንኙነትም ይሁን የፍቅር፤ ከሰዎች ጋር የምንመሰርታቸው ግንኙነቶች በህይወታችን በጣም ጠቃሚዎች ናቸው። ነገር ግን ብዙ ፈተናዎችንም ይዘው ይመጣሉ።
በእነዚህ ግንኙነቶች ውስጥ ሊጠቅሟችሁ የሚችሉ ጥቂት ነጥቦችን ይዘን ቀርበናል።

1. ግጭት ሲፈጠር አይደናገጡ

ሁሌም ቢሆን ግጭትን የምናስተናግድበት መንገድ ወሳኝነት አለው። የተለያዩ ሃሳቦች እና ፍላጎቶች ሁሌም ወደ ግጭት ሊያመሩ ይችላሉ።