Friday, July 6, 2018

ፓርላማው በሽብርተኝነት የተፈረጁ ሦስት ድርጅቶችን ፍረጃ አነሳ


የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሐሙስ ሰኔ 28 ቀን 2010 ዓ.ም. ባደረገው መደበኛ ስብሰባ፣ ሦስት ድርጅቶችን ከአሸባሪነት ለማንሳት የቀረበለትን የውሳኔ ሐሳብ በሙሉ ድምፅ አፀደቀ፡፡
የሽብርተኝነት ፍረጃ የተነሳላቸው ድርጅቶች አርበኞች ግንቦት ሰባት፣ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) እና የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) ናቸው፡፡
የውሳኔ ሐሳቡ ‹‹ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ የተጠቀሱት ድርጅቶች አመራሮችና አባላት በሰላማዊና ሕጋዊ መንገድ እንንቀሳቀሳለን በማለታቸው፣ ይኼንንም መንግሥት ያመነበት በመሆኑ…፣›› ፍረጃውን ለማንሳት አስፈላጊ መሆኑን ያመላክታል፡፡

No comments:

Post a Comment