Monday, July 30, 2018

አቡነ ጴጥሮስ በኢጣልያኖች በአደባባይ ሲገደሉ ሂደቱ እና በዕለቱ የታዩት ክስተቶች ምን ይመስሉ ነበር?


የጣልያንን ወረራ ለመከላከል  1928 አዋጅ በታወጀ ጊዜ በወቅቱ የምስራቅ ኢትዮጵያ ጳጳስ የነበሩት አቡነ ጴጥሮሥ ንጉሠነገሥቱን ተከትለው ወደማይጨው ዘመቱ። 1928 ሐምሌ21 ቀን የተባበሩት የአርበኞች ግምባር አዲስ አበባ ላይ የሠፈረውን የጠላት ጦር ለመዋጋት በአደረገው ቀጠሮ መሠረት አቡነ ጴጥሮሥ በነደጃዝማች አበራ ካሣ ይመራ ከነበረው የሠላሌ ጦር አብረው ወደ አዲስ አበባ ገቡ። ይህ ጦር ግን የሚፈለገው ውጤጥ አለመምጣቱን በመገንዘብ ወደመጣበት ሢያፈገፍግ አቡነ ጴጥሮሥ የአዲስ አበባን ህዝብ ሠብከው በጠላት ላይ ለማሥነሣት በማሠብ ከጦሩ ተለይተው አዲስ አበባ ቀሩ። ብዙም ሣይቆዩ አንድ ቀን ብቻ እንደቆዩ የጦር አለቆች ፊት ቀረቡ።

‹‹ከእኔ ክስና እስራት በስተጀርባ በመንግሥት ውስጥ ጡንቻቸው የጠነከረ ማፊያዎች ነበሩ››



አቶ መላኩ ፈንታ፣ የቀድሞ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር


የዛሬው የቆይታ አምድ እንግዳ አቶ መላኩ ፈንታ ናቸው፡፡ 50 ዓመት ጎልማሳው አቶ መላኩ 1981 .. ጀምሮ እስከ 2005 ድረስ በተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ውስጥ ከጀማሪ ኤክስፐርትነት እስከ ሚኒስትርነት ባሉ ኃላፊነቶች ከመሥራታቸው በተጨማሪ፣ በሠሩባቸውና በመሯቸው ተቋማት ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ለውጥ በማምጣት የተመሠከረላቸው ናቸው፡፡ በተለይ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣንን በሚኒስትር ማዕረግ በዋና ዳይሬክተርነት መምራታቸው ይታወሳል፡፡ 2005 .. ግንቦት ወር ጀምሮ በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረውና ክስ ተመሥርቶባቸው ለአምስት ዓመታት እስከ ግንቦት ወር 2010 .. ድረስ ታስረው ቆይተዋል፡፡ በቂ መረጃ ሳይሰበስብ ከሁለት ወይም ከሦስት ክሶች መብለጥ የሌለባቸውን ክሶች አብዝቶ በመክሰስ ዜጎችን ለእስር መዳረግ ተገቢ አለመሆኑን፣ ለፖለቲካ ፍጆታ ተብሎ ዜጎች ያለ ወንጀላቸው በወንጀል ተፈርጀው መታሰራቸው የፖለቲካ ምኅዳሩን ከማጥበብና ሰላምን ከማደፍረስ የዘለለ ሚና እንደሌለው መንግሥት ገልጾ፣ የበርካታ እስረኞች ክስ እንዲቋረጥና በይቅርታ እንዲፈቱ ሲያደርግ ለመጨረሻ የቅጣት ውሳኔ የተቀጠሩት አቶ መላኩም ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር ተፈትተዋል፡፡ ባለትዳርና የአራት ልጆች አባት የሆኑትን አቶ መላኩ በትምህርት፣ በሥራ፣ በእስር ስላሳለፏቸው ጊዜያትና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ከሪፖርተር ጋዜጣ ጋር ያደረጉትን እንሆ።

Thursday, July 26, 2018

እጅግ አሳዛኝ እና አስደንጋጭ ዜና

የሕዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ስመኘው በቀለ ዛሬ (ሐሙስ ሐምሌ 19 ቀን 2010 ዓ.ም.) ጠዋት አዲስ አበባ አብዮት አደባባይ በመኪናቸዉ ዉስጥ ሞተዉ ተገኙ፡፡

Tuesday, July 24, 2018

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሕክምና ከየት እስከ የት



በባህላዊ የሕክምና ጥበብ ድልድይ ተሻግሮ ለተዓምር የቀረቡ ፈውሶችን መስጠት የቻለው ዘመናዊ ሕክምና ወደ ኢትዮጵያ የገባው ቆይቶ ነበር፡፡ ጉንፋን ሲይዘው ዳማከሴ ጨምቆ፣ አላስቆም አላስቀምጥ ለሚለው ጥርሱ ስራስር ነክሶ፣ ለሚያዋክበው ቁርጠት ጤና አዳም ጨምቆ፣ ክፉ መንፈስ ተጠናወተኝ ሲል በየሃይማኖቱ ፀልዮ፣ ድኝ ታጥኖ ሌላም ድንገተኛና አጣዳፊ ሕመም ሲያጋጥመው ቅጠል መበጠስ ለሚቀናው የኅብረተሰብ ዘመናዊ ሕክምና ብዙም አንገብጋቢ ጉዳይም አልነበረም፡፡

የቁንጅና ሚዛን


ቁንጅና እንደየማኅበረሰቡ ባህልና እሴት ሲያልፍም እንደ ዘመኑ የአስተሳሰብ ደረጃ ትርጉሙ ይለያያል፡፡ በአንድ ወቅት የቁንጅና ተምሳሌት የነበሩ ነገሮች ዘመን ሲለወጥ ትርጉማቸውም አብሮ ሲለወጥ ይስተዋላል፡፡ በየዘመናቱ በነበረው የሥልጣኔ ደረጃ የቁንጅና አረዳድ ሁኔታ ሰዎች ውብ ሆኖ ለመታየት ብዙ ነገሮችን ያደርጉም ነበር፡፡

Monday, July 23, 2018

ኢትዮጵያ እና ኤርትራ የወዳጅነት ጨዋታ ሊያደርጉ ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከኤርትራ አቻው ጋር በነሐሴ ወር አጋማሽ አስመራ ላይ የወዳጅነት ጨዋታ ሊያደርግ ነው።የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሁለቱን ሀገራት ወንድማማችነት ለማጠናከር አስመራ ከተማ ላይ የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ ባሳለፍነው ሳምንት ደብዳቤ መላኩ ይታወሳል።

በ50 የዓለማችን አገራት የኤችአይቪ ስርጭት ጨምሯል


50 የተለያዩ የዓለማችን አገራት የኤችአይቪ ኤድስ ስርጭት እየጨመረ መምጣቱንና በቫይረሱ እየተጠቁ ካሉት ሰዎች ግማሽ ያህሉ የመድሃኒትና የህክምና አገልግሎቶችን እያገኙ እንዳልሆነ ዩኤንኤድስ የተባለው አለማቀፍ ተቋም ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል፡፡

ድምፃዊ ኤፍሬም ታምሩ የቅጅ መብት ሕግ ጥሷል ተብሎ የፍትሐ ብሔር ቅጣት ተወሰነበት


ድምፃዊ ኤፍሬም ታምሩ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 410/96 እና የተሻሻለውን አዋጀ ቁጥር 872/2007 አንቀጽ (41) ተላልፏል ተብሎ፣ የተመሠረተበትን የፍትሐ ብሔር ክስ ማስተባበል ባለመቻሉ ቅጣት ተወሰነበት፡፡

Sunday, July 22, 2018

570 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በህገ-ወጥ መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ጅግጅጋ ሲጓጓዝ ተያዘ


570 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በህገ-ወጥ መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ጅግጅጋ ሲጓጓዝ በቁጥጥር ስር መዋሉን የምስራቅ ሸዋ ዞን ፖሊስ አስታወቀ።

ባለፉት ቀናት በተከናወነ ኦፕሬሽን 10 ሚሊየን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ መያዙን ፖሊስ ገለፀ

ጥናትን መሰረት በማድረግ ባለፉት ጥቂት ቀናት በአዲስ አበባ እና ከአዲስ አበባ ውጪ በተከናወነ ኦፕሬሽን በህገወጥ መንገድ የተያዘ 10 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ መያዙን የፌደራል ፖሊስ ገለፀ።

ሰማይና ምድር በምስክርነት


አንድ ነጋዴ የተለያዩ እቃዎችን በአጋሰሶቹ ጭኖ በጉዞ ላይ እንዳለ ሶስት ቀማኞች ከመንገድ ጠብቀው እቃዎቹንና ብሩን ይዘርፉታል፡፡ነጋዴውም በፍርድ አሰጣጥ ችሎታቸውና በዘዴኝነታቸው ታዋቂ ወደነበሩት ፊታውራሪ ሃብተገወርጊስ ወይም አባ መላ ችሎት በመቅረብ በደሉን ያሰማል፡፡

Saturday, July 14, 2018

አሜሪካዊያን ከፈጣሪ ይልቅ በመከላከያና ፖሊስ ሰራዊታቸው ያምናሉ



Americans who trust the:
Military: 74%
Police: 54%
Church: 38%

እርስዎ በቀን ምን ያክል ደቂቃዎችን በማንበብ ያሳልፋሉ?



እስኪ አውሮፓዊያን በአማካኝ ምን ያክል ደቂቃዎችን በማንበብ እንደሚያሳልፉ እናካፍልዎ፡፡

Average minutes spent reading books per day, 2015.

Estonia: 13
Finland: 12

Poland: 12

ዶክተር አብይ አህመድ በ BBC አልጀዚራና ሌሎች አለም አቀፍ ሚዲያዎች እይታ

የዶክተር አብይ የመቶ ቀናት መቶ ሰበር ዜናዎች


1. መጋቢት 24 - ኢትዮጵያዊነት፣ ፍትህ፣ እኩልነት የታወጀበት የበአለ-ሲመት ንግግር
2.
መጋቢት 25 - ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ህብረት ጋር የጀመረቻቸውን ስራዎች እንደምትቀጥል የተገለፀበት
3.
መጋቢት26 - ከፕ/ አልሲ ጋር በስልክ አወ\ የደስታ መግለጫ ተለዋወጡ
4.
መጋቢት 28 - እስረኞች የተፈቱበትና ማዕከላዊ በይፋ የተዘጋበት
5.
መጋቢት 29 - የመጀመሪያው ህዝባዊ መድረክ በጅግጅጋ
6.
ሚያዚያ 02 - የኬኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርን በፅ/ቤታቸው ተቀብለው ማነጋገር
7.
ሚያዚያ 03 - ህዝባዊ መድረክ በአምቦ

ለኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በብሔራዊ ቤተ መንግስት የተዘጋጀ ዝግጅት ላይ የተደረገ የስጦታ ፕሮግራም


የከተማ አስተዳደሩ ዋና ኦዲተር ትልልቅ ጉድለቶችን ለከተማው ምክር ቤት አቅርቧል፡፡


1. ከደንብና መመሪያ ውጭ የተፈጸመ ግዥ……….…112 ሚሊየን ብር በላይ
2. በወቅቱ ያልተሰበሰበ…………..............….329 ሚሊዬን ብር በላይ

3. ጥሬ እቃ ተሰጥቶ ምላሽ ያልተደረገ……......41 ሚሊዬን ብር በላይ
4.
ለማን እንደሚከፈል የማይታወቅ ተከፋይ ሂሳብ….123 ሚሊዬን ብር በላይ